ከእሱ በፊት እንደነበሩት እንደ ኢንተርኔት እና ኤሌክትሪክ ሁሉ፣ የአይ ኤ (AI) ተስፋም የሚመካው ፍትሐዊ በሆነ ስርጭት ላይ ነው። ለሰዎች እና ለፕላኔታችን ጥቅማ ጥቅሞችን ማድረስ ደህንነቱ የተጠበቀ አጠቃቀምን በሰፊው ደረጃ ለማስቻል አዲስ መልክ የተሰጣቸው አጋርነቶችን ይጠይቃል።
በኬንያ እና በጣሊያን መንግሥታት እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) በጋራ የተዘጋጀው የናይሮቢ የአይ ኤ ፎረም 2026፣ በመላው አፍሪካ የአይ ኤ አጠቃቀምን፣ መሠረተ-ልማትን እና ሁሉን አቀፍ ተፅዕኖን ለማሳደግ ተደማጭነት ያላቸውን ዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ ባለድርሻ አካላትን በሁለት ቀናት መርሃ-ግብር (ከየካቲት 2 እስከ 3 ቀን 2018 ዓ.ም / እ.ኤ.አ. 9-10 ፌብሩዋሪ 2026) ሰብስቧል።
ፎረሙ ትኩረቱን ያደረገው ድንበር ተሻጋሪ አጋርነቶችን እና የፋይናንስ ሞዴሎችን በማፋጠን ላይ ሲሆን፣ ይህም ለአካባቢ ተስማሚ እና ሉዓላዊ የአይ ኤ መሠረተ-ልማትን ለማስቻል ነው—የአፍሪካን የተፈጥሮ ሀብት ብልጫዎች ሁሉን አቀፍ የሰው ልጅ ልማትን ወደሚደግፉ አዳዲስ የኢንዱስትሪ ኢኮኖሚዎች ለመቀየር ያለመ ነው።








